ፕሪቶሪያ በሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ አዘጋጅነት ከጃንዋሪ 25-27 ቀን 2018 ድረስ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሲካሄዱ የነበሩ የሀይማኖት መሪዎች ፣የሙሁራን እና የቢዝነስ ማህበረሰቡ አጠቃላይ የተሳተፉአቸው የውይይት መድረኮች ተጠናቀቁ ፡፡ በሀይማኖት ተቋማት የመሪዎች መድረክ ላይ ተሳታፊ የነበሩ መሪዎች ስብሰባውን አስመልክተው የሰጡትን አስተያየት በዚሁ የኢንተርኔት ሬዲዮ እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል፡፡
በሶስቱም መድረኮች ኮሚኒቲው ለእርስ በእርስ እንዲሁም ለሀገራቸው የሰላም እና የልማት አጀንዳዎች ዙሪያ መሰለፍ በሚችሉባቸው ጉዳዮች፣ የህገወጥ የሰዎች ዙውውርን ለማስቆም በሚደረገው ጥረት የዲያስፓራውን ተሳትፎ አስመልክቶ እንዲሁም የኤምባሲውን አገልግሎት አስመልክቶ ሰፋ ያሉ ውይይቶች አካሂደዋል፡፡